ለክቡር ዶ /ር ተስፋዬ አበበ ከከተማ መስተዳድሩ የተበረከተ ስጦታ

ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ ከንቲባ እንዲሁም ረዳት ፐሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ ከከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በ18/12/2011 ዓ.ም ላለፉት 65 ዓመታት በኪነጥበብ አለም ለሃገር ያበረከቱትን ታላቅ ሥራን እና ለ50 ዓመታት በፅናት የጥበብ ፍቅር ያላቸውን ወጣቶች በነፃ በማስተማር እና በስነ ምግባር የታነፁም እንዲሆኑ ላበረከቱት እጅግ የተደነቀ እና የተከበረ አገልግሎታቸው ክቡር ዶ/ር ተስፋዬ አበበን እና ማዕከላቸውን በመጎብኘት ያላቸውን ክብር እና አድናቆት የገለፁ ሲሆን ለሀገር ታላቅ ተግባር ከፈፀሙ ኢትየኢትዮጵያዊያን አንዱ እንደሆኑ እና ለእዚህን ያህል ዐመታት በነፃ ማስተማር እና ዘመን ተሻጋሪ የጥበብ ስራዎችን በጥምር ማበርከት እጅግ ከባድ እና ፈታኝ እንደሆነ በመግለፅ እና በማመስገን ቢዘገይም የከተማ አስተዳደራቸው አሁን ከ24 ዓመታት በላይ በከፍተኛ ድጋፍ እና ቀናነት የማስተማሪያ ክፍል በመስጠት አጋርነቱን ከሰጣቸው የአፍሪካ አንድነት ትምህርት ቤት ተቀያሪ ቦታ እንደሚሰጣቸው ሲያበስሩ በአዳራሹ የነበሩት አንጋፋ እና ወጣት ታዋቂ የማዕከሉ ውጤት የሆኑ አርቲስቶች አንዲሁም አሁን በመማር ላይ ያሉ በርካታ ተማሪዎች በሰሙት ዜና ተደስተው በጬኸት ፣ በለቅሶ የአባታቸው የዘመናት ልፋት መልስ በማግኘቱ አፀፋውን ሲሰጡ የነበረው ትዕይንት አስገራሚ የነበረ ሲሆን ለከንቲባው ያለቸውንም ፍቅር በማቀፍ እና በማመሥገን ፎቶግራፍ አብሮ ለመነሣት የነበረው ርብርብ አስደናቂ ነበር ፡፡
ክቡር ደ/ር ተስፋዬ አበበም የከተማ አስተዳደሩ ለደረገላቸው ነገር ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል ፡፡ በመማሪያ ክፍሏ ውስጥም ኢትዮጵያ የተሰኘው የፋዘር ስራ የሆነው ዜማ በተማሪ ዘማሪያን ቀርቧል፡፡ ረዳት ፐሮፌሰር ነብዩ ባዬም ለፋዘር ያላቸውን ክብር በሚገባ ከገለፁ በኋላም እንኳን ደስ ያለህ በማለት የተመለከቱት ዘመን ተሻጋሪ የሆነውን ኢትዮጵያ የተሰኘውን ከኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመቀጠል ህዝብ በጋራ የሚያዜመውን የፋዘርን ታላቅ ሥራ ጷግሜ 3 ቀን በሚከበረው ብሔራዊ የክብር እና
የኩራት ቀን እንዲቀርብ እድሉን ሰጥተዋል ተማሪዎችን በመወከልም አርቲስት ይገረም ደጀኔ ከንቲባውን ያመሠገነ እና ለሙያ አባቱ ለፋዘርም እንኳን ደስያለህ በማለት በቀጣይም የ50 አመታት የማስተማር ጉዞውን እና የ80ኛ ዓመት የልደት በዓሉን በመሥከረም ወር በእኛ በተማሪዎችህ በደማቅ ሁኔታ እናከብርልሃለን በማለት ቃልበመግባት የዕለቱ ፕሮግራም መዝጊያም ” መማር ያስከብራል ሀገርን
ያኮራል” በሚለው የፋዘር ዜማ በተማሪዎቹ ሲቀርብ ከንቲባውም ጭምር በማዜም ተጠናቋል ፡፡
ለተሠጠን ክብር ደግመን ደጋግመን የከተማ አስተዳደሩን እናመሠግናለን!!!

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *